የእስራኤልም ልጆች ከባዕድ ሕዝብ ሁሉ ራሳቸውን ለዩ፤ ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ተናዘዙ።
መዝሙር 51:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ መተላለፌን ዐውቃለሁና፤ ኀጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ስሕተቴን ዐውቃለሁ፤ የኃጢአቴንም ብዛት ዘወትር እገነዘባለሁ። |
የእስራኤልም ልጆች ከባዕድ ሕዝብ ሁሉ ራሳቸውን ለዩ፤ ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ተናዘዙ።
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
ዐመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኀጢአታችንም መስክሮብናልና፥ ዐመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድቅንም አላወቅንምና።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።”