ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከንፈሮቹ ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከንቱ ያመልኩኛል፤ ሰው ሠራሽ ትምህርትም ያስተምራሉ፤
መዝሙር 50:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አትወድድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤ “ሕጌን ለማነብነብ፣ ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉውን ግን እግዚአብሔር አለው፦ ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ? ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትይዛለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤ “ሕጌን ለማንበብ፥ ቃል ኪዳኔን በአንደበትህ ለመግለጽ ምን መብት አለህ? |
ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከንፈሮቹ ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከንቱ ያመልኩኛል፤ ሰው ሠራሽ ትምህርትም ያስተምራሉ፤
ነገር ግን ለሌላ ሳስተምር፥ እኔ ለራሴ የተናቅሁ እንዳልሆን ሰውነቴን አስጨንቃታለሁ፥ ሥጋዬንም አስገዛዋለሁ።
እጃቸውን ይዤ ከምድረ ግብፅ ባወጣኋቸው ጊዜ ለአባቶቻቸው እንደ ገባሁት እንደዚያ ያለ ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልኖሩምና፤ እኔም ቸል ብያቸዋለሁና” ይላል እግዚአብሔር።