የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ ድረስልኝ ብዬ ስጮኽ ስማኝ።
አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ መቃተቴንም አስተውል፥
ንጉሤና አምላኬ ሆይ! ወደ አንተ ስለምጸልይ ለእርዳታ የምጮኸውን ጩኸት አድምጥ።
አቤቱ አምላኬ ሆይ! ወደ ባሪያህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፤ ዛሬም ባሪያህ በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎት ስማ፤
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች።
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ከተቀደሰ ተራራውም ሰማኝ።
ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና፥ ተከናወን፥ ንገሥም፤ ቀኝህም በክብር ይመራሃል።
ለስሙም ዘምሩ፥ ለክብሩም ምስጋናን ስጡ።
መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፤ ከቍጣህ መቅሠፍት ተመለስህ።
አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና ቸል አይለንም፤ እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችን ነው። እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር ያድነናል።
አንተ ድምፄን ሰማህ፤ ጆሮህንም ከልመናዬ አትመልስ።