አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
መዝሙር 41:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁልጊዜ፥ “አምላክህ ወዴት ነው?” ይሉኛልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ምሕረት አድርግልኝ፤ የእጃቸውን እንድከፍላቸው አስነሣኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞ የሰላሜ ሰው፥ የታመንሁበት እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ማረኝ፤ በጠላቶቼም ላይ ብድሬን እመልስ ዘንድ ጤንነቴንም መልስልኝ፤ |
አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
ነፍሴን ከሞት፥ ዐይኖቼን ከዕንባ፥ እግሮቼንም ከድጥ አድነሃልና፥ በሕያዋን ሀገር እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ።
በእኔ ላይ የተሰበሰቡና የከበቡኝን የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፤ መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እንነሣለን” ይላሉ።
የተማማልሃቸው ሰዎች ሁሉ ወደ ዳርቻህ ሰደዱህ፤ የተስማሙህም ሰዎች ተነሡብህ፤ አሸነፉህም፤ በበታችህም አሽክላ ዘረጉብህ፤ እነርሱም ማስተዋል የላቸውም።