መዝሙር 40:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እንደ ወደድኸኝ ዐወቅሁ። ጠላቶቼ በእኔ ደስ አላላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አትንፈገኝ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዳኝ ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሰወርኩም፥ ታማኝነትህንና ማዳንህንም ተናገርሁ፥ ጽኑ ፍቅርህንና እውነትህን ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ፤ ፍቅርህና ዘለዓለማዊ ታማኝነትህ ለዘለዓለም ይጠብቁኝ። |
በጦራቸው ምድርን አልወረሱም፥ ክንዳቸውም አላዳናቸውም፤ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፤ ይቅር ብለሃቸዋልና።
መድኃኒቴ በእግዚአብሔር ነው፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ነው፥ የረድኤቴ አምላክ፥ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።