መዝሙር 39:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤ የሞኞች መሣለቂያ አታድርገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ አሁንስ ማንን እጠብቃለሁ? ተስፋዬ በአንተ ነው።። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኃጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤ ሞኞች እንዲሳለቁብኝ አታድርግ። |
የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናት በወለሉና በምሥዋዑ መካከል እያለቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕዝብህ ራራ፤ አሕዛብም ይገዙአቸው ዘንድ ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብም መካከል፦ አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።
እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን፥ “እነሆ እህልንና ወይንን፥ ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፤ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።
መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።