ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግ ጭቃም አወጣኝ፥ እግሮቼንም በዓለት ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።
እንደ ዲዳ ዝም አልሁ፤ ለበጎ ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ ሆኖም ጭንቀቴ ባሰ።
በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፥ ክፉ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ ሁሉ በአፌ ላይ ልጓም አኖራለሁ አልሁ።
አንድ ቃል እንኳ ሳልናገር ዝም አልኩ፤ መልካም ስለ ሆነ ነገር እንኳ አልተናገርኩም፤ ነገር ግን ሥቃዬ ከበፊት ይልቅ እየባሰ ሄደ።
ሰውነቴ በላዬ ላይ ባለቀች ጊዜ አቤቱ፥ መንገዴን አንተ ታውቃለህ፤ በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
ለወዳጆቼና ለወንድሞቼ እንደማደርግ አደረግሁ፤ እንደሚያለቅስና እንደሚተክዝ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ።
እርሱ ግን በመከራው ጊዜ አፉን አልከፈተም፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።
እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም እንል ዘንድ አንችልም።”