ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥ እጅህንም በእኔ ላይ አክብደህብኛልና።
እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፤ እንደ ለምለም ቅጠልም ይጠወልጋሉ።
እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥ እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና።
እንደ ሣር ቶሎ ይደርቃሉ፤ እንደ ቅጠልም ጠውልገው ይረግፋሉ።
እንደ አበባ ይወጣል፥ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላም ያልፋል፥ እርሱም አይኖርም።
ዘመኑ ለክፉዎች አይሆንምና የኃጥኣንም መብራት ይጠፋልና።
“ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤