በጠላቴ እጅ አልዘጋኸኝም፥ በሰፊም ስፍራ እግሮቼን አቆምህ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤
አቤቱ፥ በፈቃድህ እንደ ጽኑ ተራራ አጠነከርከኝ፥ ፊትህን ስትሰውር፥ እኔም ደነገጥሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ጠራሁህ፤ ምሕረትንም ለመንኩህ።
አሁን ግን ሕማም በአንተ ላይ መጥቶ ዳሰሰህ። አንተም ተቸገርህ።
መንገዳቸው ዳጥና ጨለማ ትሁን፥ የእግዚአብሔርም መልአክ ያሳድዳቸው።