መዝሙር 30:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በትድግናህ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ። መከራዬን አይተሃልና፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣ ተራሮቼ ጸኑ፣ ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣ ውስጤ ታወከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በደስታዬ፦ ለዘለዓለም አልታወክም አልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ሞገስን በሰጠኸኝ ጊዜ እንደማይነቃንቅ ተራራ አበረታኸኝ፤ ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተስፋ ቈረጥኩ። |
እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ አይሰጠውም።
በዚያም ቀን ቍጣዬ ይነድድባቸዋል፤ እተዋቸውማለሁ፤ ፊቴንም ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም መብል ይሆናሉ፤ በዚያም ቀን፦ በእውነት አምላካችን እግዚአብሔር ትቶናልና፥ በእኛም መካከል የለምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገኘን እስኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት ይደርስባቸዋል።