ኀይሌና መጠጊያዬ አንተ ነህና ስለ ስምህ ምራኝ፥ መግበኝም፤
እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤ ወደ ጕድጓድ ከመውረድም መልሰህ ሕያው አደረግኸኝ።
አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈወስከኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤ ወደ ጥልቁም ከመውረድ ሕይወቴን ጠበቅኸው።
ነፍሴ ወደ ጥፋት እንዳትወርድ አድኖአታል፥ ሕይወቴም ብርሃንን ታያለች።’
አንጀታቸውን ቋጠሩ፥ አፋቸውም ትዕቢትን ተናገረ።
የአማልክት ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፥
ጌታ ሆይ፥ ስለ እርስዋ እንዲህ አልሁህ፤ ነፍሴን አዳንሃት፤ ደስ አለኝ፤ በሕይወትም ኖርሁ።