አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ!
ከልጁ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸ ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶቼ እንዴት ብዙዎች ናቸው! ብዙዎችም በጠላትነት በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤
አቤሴሎምና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ፥ አኪጦፌልም ከእርሱ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ምድርም ተንቀጠቀጠች፥ ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔር ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።
ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ፤ ይገድሉአቸውማል።
ሕዝቡም ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፤” አሉ።
እነዚህም ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበው መጡ፤ እስራኤልንም በማሮን ውኃ አጠገብ አንድ ሆነው ተያያዙአቸው።