“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
መዝሙር 27:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፥ ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤ መቼም ረዳቴ ነህና። አዳኝ አምላኬ ሆይ፤ አትጣለኝ፤ አትተወኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባርያህ ፈቀቅ አትበል፥ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተወኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላኬና አዳኜ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ፤ ተቈጥተህም እኔን አገልጋይህን ከአንተ እንድርቅ አታድርገኝ፤ ረዳቴም ስለ ሆንክ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
ሰነፍ በልቡ፥ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉም፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም። አንድም እንኳ የለም።
በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤ አንተ አምላኪዬና መድኀኒቴ ነህና፥ ዘወትርም አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ለይታለች፤ ይቅርም እንዳይላችሁ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።
ከእነርሱም እንዳልመለስ፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።
ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በመሴፋና በአሮጌው ከተማ መካከል አኖረው፤ ስሙንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድኤት ማለት ነው።