እግዚአብሔር ረዳቴና መታመኛዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ፥ እርሱም ይረዳኛል፤ ሥጋዬም ለመለመ፥ ፈቅጄም አምነዋለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤ ራራልኝ፤ ስማኝም።
አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፥ ማረኝና አድምጠኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ ጮክ ብዬ ስጣራ ስማኝ! ምሕረትን አድርግልኝ፤ ጸሎቴንም ስማ!
እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ ኀጢኣተኛ እንድሆን አታስተምረኝ፤ ለምንስ እንደዚህ ፈረድህብኝ?
ሁሉ ተስተካክሎ በአንድነት ዐመፀ፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም፤ አንድም እንኳ የለም።
በጠላቶቼ ሁሉ ዘንድ ተሰደብሁ፥ ይልቁንም በጎረቤቶቼ ዘንድ፥ ለዘመዶቼም አስፈሪ ሆንሁ፤ በሜዳ ያዩኝም ከእኔ ሸሹ።
የኃጥኣን መቅሠፍታቸው ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን ይቅርታ ይከባቸዋል።
እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ጽድቄን ሰማኝ፥ ከጭንቀቴም አሰፋልኝ፤ ይቅር አለኝ፥ ጸሎቴንም ሰማኝ።
የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።