ክፉዎች ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ የሚያሠቃዩኝ እነዚያ ጠላቶቼ ደከሙ፥ ወደቁም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤ መርምረኝም፤ ልቤንና ውስጤን መርምር፤
አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፥ ኩላሊቴንና ልቤን መርምር።
እግዚአብሔር ሆይ! ፈትነኝ፤ ምኞቴንና ሐሳቤንም መርምር።
ኀጢአቶችና በደሌ ምን ያህል ናቸው? ምን ያህል እንደ ሆኑ አስታውቀኝ።
እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ከጠላቶቼ እድናለሁ።
የኃጥኣን ክፋት ያልቃል፥ ጻድቃንን ግን ታቃናቸዋለህ፤ እግዚአብሔር ልቡናንና ኵላሊትን ይመረምራል።
አቤቱ! ጽድቅን የምትፈትን ኵላሊትንና ልብን የምትመረምር የሠራዊት ጌታ ሆይ! ክርክሬን ገልጬልሃለሁና ፍረድልኝ።
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።