እግዚአብሔር ቸር ጻድቅም ነው፤ ስለዚህ የሚሳሳቱትን በመንገድ ይመራቸዋል።
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኀያል፤ እግዚአብሔር ነው በውጊያ ኀያል።
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ጌታ ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ ጌታ ነው፥ በሰልፍ ኃያል።
ይህ የክብር ንጉሥ ማነው? እርሱ ብርቱና ኀያሉ እግዚአብሔር ነው። እርሱ በጦርነት ኀያሉ እግዚአብሔር ነው።
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት ኀጢአቴን ደምስስ።
ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥ እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው።
እግዚአብሔር ጦርነትን ያጠፋል፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው፤
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
አለቆችንና ገዢዎችን በመግፈፉ በግልጥ አሳያቸው፤ ራቁቱን በመሆኑም አሳፈራቸው።
አየሁም፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ ድልም እየነሣ ወጣ፤ ድል ለመንሣት።