አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አልሰማኸኝም። በሌሊትም በፊትህ አላሰብከኝም።
የልቡን መሻት ሰጠኸው፤ የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም። ሴላ
አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፥ በማዳንህም እንዴት አብዝቶ ሐሤትን ያደርጋል!
የልቡን ምኞት ሰጥተኸዋል፤ የለመነህንም አልከለከልከውም።
ኀጢአቴ ከራሴ ጠጕር በዝቷልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዶአልና።
ዘወትር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሊያድናቸው ይቻለዋል፤ ለዘለዓለምም ሕያው ነውና ያስታርቃቸዋል።
ሐናም ጸለየች፤ እንዲህም አለች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በአምላኬ በመድኀኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህም ደስ ብሎኛል።