መዝሙር 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ ዐወቅሁ፤ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል በቀኙ የማዳን ኀይል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤ ዑደቱም እስከ ሌላው ዳርቻ ነው፤ ከትኵሳቱም የሚሰወር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፥ እንደ አርበኛ በመንገዱ መሮጥ ደስ ይለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንዱ የሰማይ ዳርቻ ተነሥቶ ወደ ሌላው የሰማይ ዳርቻ ይገሠግሣል፤ ከሙቀቱም ኀይል ሊደበቅ የሚችል ምንም ነገር የለም። |
እንግዲህ ከሰማችሁት ከሰማይ በታች በመላው ዓለም ከተሰበከው እኔ ጳውሎስም አዋጅ ነጋሪና መልእክተኛ ሆኜ ከተሾምሁለት፥ ከወንጌል ትምህርት ተስፋ የመሠረታችሁ አቅዋም ሳይናወጥ ጨክናችሁ በሃይማኖት ብትጸኑ፥
አቤቱ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፤ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኀይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፤ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።