መዝሙር 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳን ላይ ተገለጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምላሱ የማይሸነግል፤ በባልንጀራው ላይ ክፉ የማይሠራ፤ ወዳጁን የማያማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ የሚቀርቡትን የማይሰድብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች ሰዎችን የማያማ፥ በጓደኞቹ ላይ ክፉ ነገር የማያደርግ፥ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታን የማያሠራጭ፥ |
ይህን የሚያደርግ በእርሱም ጸንቶ የሚኖር፥ ሰንበታትንም የሚጠብቅና የማያረክስ፥ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ሰው ብፁዕ ነው።”
ሐሜተኞች፥ እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ተሳዳቢዎች፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክሕተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸውም የማይታዘዙ ናቸው።
ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም።
እነሆ፥ ዛሬ በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ እንደ ሰጠህ ዐይንህ አይታለች፤ አንተንም እንድገድልህ ሰዎች ተናገሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእግዚአብሔር የተቀባ ነውና እጄን በጌታዬ ላይ አልዘረጋም ብዬ ራራሁልህ።