ወደ ሜዳም አወጣውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ከዋክብትን ቍጠራቸው። ዘርህም እንደዚሁ ነው” አለው።
መዝሙር 147:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃሉን ወደ ምድር ይልካል፥ ነገሩም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤ እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከዋክብትን ብዛት ቈጥሮ ያውቃል፤ እያንዳንዳቸውንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። |
ወደ ሜዳም አወጣውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ከዋክብትን ቍጠራቸው። ዘርህም እንደዚሁ ነው” አለው።
ዐይናችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? ከዋክብትንም በሙሉ የሚቈጥራቸው እርሱ ነው፤ በየጊዜያቸው ያመጣቸዋል፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በክብሩ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።