አፋቸውም ከንቱ ነገርን ከሚናገር፥ ቀኛቸውም የዐመፃ ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አድነኝ፥ አስጥለኝም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራ አውጣት።
አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፥ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ክብርህ ሕይወቴን ጠብቅ፤ በእውነተኛነትህም ከችግሬ ሁሉ ነጻ አውጣኝ።
ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
ለእጆቼ ጠብን፥ ለጣቶቼም ሰልፍን ያስተማራቸው አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን፤
እኔ ግን በየዋህነቴ እኖራለሁ፤ አቤቱ፦ አድነኝ ይቅርም በለኝ።
ኀጢአታቸው የተተወላቸው፥ በደላቸውንም ሁሉ ያልቈጠረባቸው ብፁዓን ናቸው።
በግፍ የሚጠሉኝ በላዬ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጠሉኝና በዐይናቸው የሚጠቃቀሱብኝም።
ሕዝብህን በጽድቅ፥ ድሆችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።
አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ የልመናዬንም ቃል ስማ።
አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።