አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፤ በአንተ ታመንሁ፥ ነፍሴን አታውጣት።
እግዚአብሔር ሆይ፤ የክፉዎች ምኞት አይፈጸም፤ በትዕቢትም እንዳይኵራሩ፣ ዕቅዳቸው አይሳካ። ሴላ
አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጉልበት፥ በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ።
ለክፉዎች የሚፈልጉትን ነገር አትስጣቸው፤ ዕቅዳቸው እንዲሰምር አታድርግ።
አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም፥ “አቤቱ የአኪጦፌልን ምክር ለውጥ” አለ።
አቤቱ፥ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥ ጻድቃንህም ያመሰግኑሃል።
ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።