ጻድቃን ግን በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ፤ ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።
አንተ ውስጣዊ ሰውነቴን ፈጥረሃልና፤ በእናቴም ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ።
አቤቱ፥ አንተ ኩላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል።
ሁለንተናዬን የፈጠርክ አንተ ነህ፤ በእናቴ ማሕፀን አገጣጥመህ የሠራኸኝ አንተ ነህ።
እኔን በማኅፀን የፈጠረ እነርሱንስ የፈጠረ አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ የሠራን አንድ አይደለምን?
እንደ ጠል በባዘቶ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይወርዳል።
እምነትና በጎነት በፊቱ፥ ቅድስናና የክብር ገናናነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።
የፈጠረህ ከማኅፀንም የሠራህ የሚረዳህም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፥ “ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ወዳጄ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ።
እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከማኅፀንም ጀምሮ የተሸከምኋችሁ፥ ከሕፃንነትም ጀምሮ ያስተማርኋችሁ፥ ስሙኝ።
“በእናትህ ሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፤ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።”
አካል ሁሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ መስማት ከየት በተገኘ ነበር፤ አካልስ ሁሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ ማሽተት ከየት በተገኘ ነበር?