መዝሙር 138:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕውቀትህ በእኔ ላይ ተደነቀች፤ በረታችብኝ፥ ወደ እርሷም ለመድረስ አልችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በከፍታ ስፍራ ቢሆንም፣ ዝቅ ያለውን ይመለከተዋል፤ ትዕቢተኛውን ከሩቅ ያውቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ከፍ ያለ ነውና፥ ዝቅተኞችን ይመለከታልና፥ ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ያውቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሁሉ በላይ ከፍ ያልክ ሆነህ ሳለ፥ ትሑታንን ትንከባከባለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ሆነህ ትመለከታቸዋለህ። |
የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?
እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ይከብራልና።”
በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።