አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶች ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኀያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድም የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና።
መዝሙር 136:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማረኩን በዚያ የዝማሬ ቃል ጠይቀውናልና፥ የወሰዱንም፥ “የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን” አሉን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጌቶች ጌታ ለሆነው አምላክ ምስጋና አቅርቡ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። |
አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶች ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኀያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድም የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”