ከበኵራቸው ጋር ግብፅን የገደለ፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
ብዙ ሕዝቦችን መታ፤ ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
ብዙ አሕዛብን መታ፥ ብርቱዎችንም ነገሥታት ገደለ።
ብዙ የአሕዛብ መንግሥታትን ደመሰሰ፤ ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
እስራኤልም በሰይፍ መታው፤ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ ኢያዜር ነበረ።
እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡን ሁሉ አንድ ሰው ሳያመልጥ መቱ፤ ምድሩንም ወረሱ።