ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፤ ስድብን እጅግ ጠግበናልና፤
ኢየሩሳሌም እጅግ እንደ ተጠጋጋች፣ ከተማ ሆና ተሠርታለች።
ኢየሩሳሌምስ እርስ በርስዋ እንደ ተገጠገጠች ከተማ ተሠርታለች።
ኢየሩሳሌም እርስ በርስዋ ተጠጋግታና ተጠናክራ የተሠራች ከተማ ናት።
ዳዊትም በአንባዪቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ እርስዋም የዳዊት ከተማ ተባለች። ከተማዋንም ዙሪያዋን እስከ ዳርቻዋ ድረስ ቀጠራት፤ ቤቱንም ሠራ።
ቅጥሩንም ሠራን፤ ቅጥሩም ሁሉ እስከ እኩሌታው ድረስ ተጋጠመ፤ ሕዝቡ ከልብ ይሠራ ነበርና።
ጽዮንም ሆይ፥ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአልና።