ፀሐይ በቀን አያቃጥልህ፤ ጨረቃም በሌሊት።
ሰላምን በሚጠሉ መካከል፣ ነፍሴ እጅግ ብዙ ጊዜ ኖረች።
ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ኖረች።
ሰላምን ከሚጠሉ ሕዝቦች ጋር እጅግ ለረጅም ጊዜ ኖርኩ።
ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ ጆሮዋም እንደ ደነቈረ እባብ፥
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።
“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።
ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።