ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ፤ ለዘለዓለም አትጣለኝ።
ሰውን መከታ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
በሰው ከመታመን ይልቅ በጌታ መጠለል ይሻላል።
በሰው ከመመካት ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
ላባም፥ “የምሰጥህ ምንድን ነው?” አለው። ያዕቆብም አለው፥ “ምንም አትስጠኝ፤ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደገና በጎችህን አሰማራለሁ፤ እጠብቃለሁም።
ልባቸው የቈሰለውን ይፈውሳል፥ ቍስላቸውንም ያደርቅላቸዋል።
እኔስ፥ “አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አንተን በድያለሁና ለነፍሴ አስተስርይላት” አልሁ።