በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ ልቡ ጽኑዕ ነው፥ ለዘለዓለምም አይታወክም።
ከዘላለም እስከ ለዘላለም የጸና ነው፤ በእውነትና በቅንነትም የተሠራ ነው።
ለሁልጊዜና ዘለዓለምም የጸኑ ናቸው፥ በእውነትና በጽድቅም የተሠሩ ናቸው።
እነርሱም ለዘለዓለም የጸኑ ናቸው፤ የተሰጡትም በእውነትና በታማኝነት ነው።
አቤቱ፥ ንጉሥን አድነው፥ በምንጠራህም ቀን ስማን።
ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”
እውነት እላችኋለሁ፤ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፤ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።
እንግዲህ በእምነት ኦሪትን እንሽራለን? አንሽርም፤ ኦሪትን እናጸናለን እንጂ።
አሁንም ቢሆን ኦሪትስ ቅድስት ናት፤ ትእዛዝዋም ቅዱስና እውነት ነው፤ መልካምም ነው፤ በረከትም ነው።
“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።