በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ ሬሳዎችንም ያበዛል፤ በምድር ላይ የብዙዎችን ራሶች ይቀጠቅጣል።
ክፉ ሰው በላዩ ሹም፤ ከሳሽም በቀኙ ይቁም።
በላዩ ክፉ ሰውን ሹም፥ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም።
በእርሱ ላይ የሚፈርድ ዐመፀኛ ዳኛ ሠይም አንዱም ሰው እንዲከስሰው አድርግ፤
እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም ይከስሰው ዘንድ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።
“ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፤” አለ። እነርሱ ግን “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፤” አሉ።
አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፤ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤
ራት ሲበሉም አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ሰው በይሁዳ ልብ ሰይጣን አደረ።
እንጀራውንም ከተቀበለ በኋላ ወዲያውኑ በይሁዳ ልብ ሰይጣን አደረበት፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እንግዲህ የምታደርገውን ፈጥነህ አድርግ” አለው።