የሚረዳውንም አያግኝ፤ ለድሃ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤ የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።
አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር መውጣት አቆምህ።
የሰው ርዳታ ከንቱ ነው፤ ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ እርዳን።
“እንደዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰማሁ፤ እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ።
እግዚአብሔር እኔን ከመቅጣት አልተመለሰም፥ ከእርሱም የተነሣ ከሰማይ በታች ያሉ አናብርት ይዋረዳሉ።
እስትንፋሱ በአፍንጫው ያለበትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?
ግብፃውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
ፌ። በማያድን ወገን እያመንን ረዳታችን ከንቱ ስለ ሆነ፥ እኛ ገና በሕይወት ሳለን ዐይኖቻችን ጠፉ።