ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ በቀኝህ አድን፥ አድምጠኝም።
በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።
በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው፥
በመከራቸውም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከጭንቀታቸው አዳናቸው።
በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፤ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮዎቹ ገባ።
በእግዚአብሔር ኀይልን እናደርጋለን፤ እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል።
አቤቱ፥ ከንፈሮችን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።
አምላካችን እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ ይናገራሉ፥ በእርሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።
እስኪጠፉ ድረስ፥ ፊቴንም እስኪሹ ድረስ እሄዳለሁ፤ ወደ ስፍራዬም እመለሳለሁ።
ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።