ዳዊትም ጋድን፥ “በሁሉም እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ በሰው እጅ ከምወድቅ ይልቅ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል” አለው።
መዝሙር 106:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ችግረኛንም በችግሩ ረዳው፤ እንደ ሀገር በጎች አደረገው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአሕዛብ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ጠላቶቻቸውም በላያቸው ሠለጠኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሕዛብም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአሕዛብ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ጠላቶቻቸውም ገዥዎቻቸው ሆኑ። |
ዳዊትም ጋድን፥ “በሁሉም እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ በሰው እጅ ከምወድቅ ይልቅ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል” አለው።
ስለዚህ እነሆ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቻለሁ፤ ድርሻሽንም አጕድያለሁ፤ ለሚጠሉሽም፥ ከመንገድሽ ለመለሱሽና ለአሳቱሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።
“እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፤ በሰባት መንገድም ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ የተበተንህ ትሆናለህ።
ዕውር በጨለማ እንደሚዳብስ በቀትር ጊዜ ትዳብሳለህ፤ መንገድህም የቀና አይሆንም፤ በዘመንህም ሁሉ የተገፋህ፥ የተዘረፍህም ትሆናለህ፤ የሚረዳህም የለም።
የምድርህን ፍሬ፥ ድካምህንም ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤ አንተም ሁልጊዜ የተጨነቅህ፥ የተገፋህም ትሆናለህ።
በራብና በጥማት፥ በዕራቁትነትም፥ ሁሉንም በማጣት እግዚአብሔር ለሚልክብህ ለጠላቶችህ ትገዛለህ፤ እስኪያጠፋህም ድረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭናል።
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።
ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኢጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፥ “ገዢዎቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “እንዳደረጉባችሁ እንዲሁ አደረግሁባቸው” አላቸው።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረኳቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ማረኩአቸውም፤ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከዚያም ወዲያ ጠላቶቻቸውን ሊቋቋሙ አልቻሉም።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን በእስራኤል ላይ አበረታባቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወንዞችም መካከል ባለች በሶርያ ንጉሥ በኩሳርሳቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ለኩሳርሳቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት።