ዐውሎ ነፋሱንም ጸጥ አደረገ፥ ባሕሩም ዝም አለ።
በሥራቸውም እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ መቅሠፍትም በላያቸው መጣ።
በሥራቸውም አስመረሩት፥ ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
በክፉ ሥራቸው እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በዚህ ምክንያት መቅሠፍት በመካከላቸው ተነሣ።
እነርሱ በክፉ መከራና በጭንቀት ተሠቃዩ፥ እያነሱም ሄዱ፤
እግዚአብሔር በጊዜው ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፥ እነርሱ ግን ብዙ ዕውቀትን ይሻሉ።
እስራኤልም ለብዔል ፌጎር ራሳቸውን ለዩ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ።
ያንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። ሁለቱንም እስራኤላዊውን ሰውና ምድያማዊቱን ሴት ሆዳቸውን ወጋቸው፤ ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተወገደ።
በመቅሠፍቱም የሞቱት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ።
ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደ ሴሰኑ፥ በአንድ ቀንም ሃያ ሦስት ሺህ ሰዎች እንደ ወደቁ አንሴስን።