ወደ ሰማይ ይወጣሉ፥ ወደ ጥልቅም ይወርዳሉ፤ ሰውነታቸውም በመከራ ቀለጠች።
በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ እጁን አንሥቶ ማለ፤
በምድረ በዳም ይጥላቸው ዘንድ፥ ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥ በየአገሩም ይበትናቸው ዘንድ፥ እጁን አነሣባቸው።
ስለዚህ እጁን አንሥቶ በመማል በበረሓ የሚያጠፋቸው መሆኑን ነገራቸው፤
ሰማያት ደስ ይላቸዋል፥ ምድርም ሐሤትን ታደርጋለች፤ ባሕር ሞላዋ ትናወጣለች፤
ለአብርሃምና ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብም እሰጣት ዘንድ እጄን ወደ ዘረጋሁባት ምድር አገባችኋለሁ፤ እርስዋንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ከምድር ሁሉ ወደምታምር ወደ ሰጠኋቸው ምድር እንዳላገባቸው በምድረ በዳ በእነርሱ ላይ ፈጽሜ እጄን አነሣሁ።
ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቍጣዬ ማልሁ።”
ከካዱት በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ በማን ላይ ማለ?