ከፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፤ በባሕሩም መካከል በደረቅ ዐለፉ፤ የተከተሉአቸውን ግን ድንጋይ በጥልቅ ውኃ እንዲጣል በቀላይ ውስጥ ጣልሃቸው።
መዝሙር 106:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጨለማና በሞትም ጥላ የተቀመጡ፥ በችግር በብረትም የታሰሩ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባላጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ ከጠላትም እጅ ታደጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሚጠሉአቸውም ሰዎች እጅ አዳናቸው፤ ከጠላቶቻቸውም እጅ ታደጋቸው። |
ከፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፤ በባሕሩም መካከል በደረቅ ዐለፉ፤ የተከተሉአቸውን ግን ድንጋይ በጥልቅ ውኃ እንዲጣል በቀላይ ውስጥ ጣልሃቸው።
እግዚአብሔርም በዚያ ቀን እስራኤልን ከግብፃውያን እጅ አዳናቸው፤ እስራኤልም ግብፃውያን እንደ ሞቱ በባሕር ዳር አዩ።
በተከተሉአችሁም ጊዜ በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥ በግብፅ ጭፍራ በፈረሶቻቸውም፥ በሰረገሎቻቸውም ያደረገውን፥