በሥራቸውም አነሣሱት ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ ዓሦቻቸውንም ፈጀ።
ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥ ዓሦቻቸውንም ገደለ።
የወንዞቻቸውንም ውሃ ወደ ደም ለወጠ፤ ዓሣዎቻቸውንም ሁሉ ገደለ።
እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አልነበረም፤ ተጣራሁ፤ የሚመልስም አልነበረም፤ እጄ ለማዳን ጠንካራ አይደለምን? ወይስ ለማዳን አልችልምን? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዐሣዎቻቸው ይሞታሉ፤ በጥማትም ያልቃሉ።
ሁለተኛውም ጽዋውን በባሕር ውስጥ አፈሰሰ፤ እንደ ሞተም ሰው ደም ሆነ፤ በባሕርም ከሚኖሩት ሕይወት ያለበት ነፍስ ሁሉ ሞተ።