ድንቅንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገርንም በኤርትራ ባሕር ያደረገውን።
ይኸውም ሹማምቱን በራሱ መንገድ ይመራ ዘንድ፣ ሽማግሌዎቹንም ጥበብ ያስተምር ዘንድ ነበር።
መኰንኖቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።
በንጉሡ ባለሥልጣኖች ላይ አዛዥ ሆነ፤ ለንጉሡም አማካሪዎች ጥበብን ያስተምራቸው ዘንድ ሥልጣን ተሰጠው።
አሁንም ብልህና ዐዋቂ ሰውን ለአንተ ፈልግ፤ በግብፅ ምድር ላይም ሹመው።
ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፥ “በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰውን እናገኛለን?”
ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፥ “እኔ ራሴ ፈርዖን ነኝ፤ በግብፅ ሀገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁን አያንሣ።”
የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ይሆናሉ፤ ነገሥታትን የሚመክሩ ጥበበኞችም ምክራቸው ስንፍና ትሆናለች። ንጉሥን፥ “እኛ የጥበበኞች ልጆች፥ የቀደሙ ነገሥታትም ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ?”