መዝሙር 104:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቤቱ ጌታም አደረገው፥ በገንዘቡ ሁሉ ላይ ገዢ አደረገው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤ የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮኻሉ፥ ከእግዚአብሔርም ምግባቸውን ይሻሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሚያዘጋጀውን ምግብ ሲያድኑ የአንበሳ ደቦሎች ያገሣሉ። |
አጥንቶች ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃውን ከሚቀማው እጅ ድሃውንና ችግረኛውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።
እንግዲህ ለራሳችን ምን እንሰብስብ? የእንስሳት ጠባቂዎች አለቀሱ፤ ማሰማሪያ የላቸውምና፥ የበጎች መንጋዎችም ጠፍተዋልና።
እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ! የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኀይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ።
ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካው ውስጥ በከንቱ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ሳይዝ በመደቡ ሆኖ በከንቱ ይጮኻልን?