እንዳያልፉትም ድንበር አደረግህላቸው፥ ምድርን ይከድኑ ዘንድ እንዳይመለሱ።
እርሱ ሁልጊዜ በደልን አይከታተልም፤ ለዘላለምም አይቈጣም።
ሁልጊዜም አይከስም፥ ለዘለዓለምም አይቈጣም።
ዘወትር የሚገሥጽ አይደለም፤ ቊጣውም ለዘለዓለም አይቈይም።
በእጅህ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፤ የጽድቅ አምላክ እግዚአብሔር፥ ተቤዠኝ።
በጠብና በንቀት ይሰዳቸዋል፤ በቍጣና በክፉ መንፈስ ትገሥጻቸው ዘንድ ትጀምራለህን?
“መንፈስ ከእኔ ይወጣልና፥ የሁሉንም ነፍስ ፈጥሬአለሁና ለዘለዓለም አልቀስፋችሁም፤ ሁልጊዜም አልቈጣችሁም።
ሂድና ይህን ቃል ወደ ሰሜን ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ከዳተኛዪቱ እስራኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመለሽ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ መሓሪ ነኝና፥ ለዘለዓለምም አልቈጣምና በእናንተ ላይ ፊቴን አላጸናም፥” ይላል እግዚአብሔር።
ቍጣው ለዘለዓለም ይኖራልን? እስከ ፍጻሜስ ድረስ ይጠብቀዋልን? እነሆ እንዲህ ብለሽ ተናገርሽ፤ እንደ ተቻለሽም መጠን ክፉን ነገር አደረግሽ።”
የሠራውም ኀጢአት ሁሉ አይታሰብበትም፤ ፍርድንና ቅን ነገርን አድርጎአልና፤ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።