እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት፥ እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ በቤተ መቅደሱም አገለግል ዘንድ።
መዝሙር 101:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተቀሠፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ። እህል መብላት ተረስቶኛልና አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠማማ ልብ ከእኔ ይርቃል፤ ለክፋትም ዕውቅና አልሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠማማ ልብም ከእኔ ይርቃል፥ ክፉን አላውቀውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠማማ ልብ ያላቸው ሰዎች ከእኔ ይራቁ፤ ከክፋትም ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም። |
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት፥ እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ በቤተ መቅደሱም አገለግል ዘንድ።
በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሸሽጎኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሰውሮኛልና፥ በዓለትም ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።