መዝሙር 100:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠማማ ልብም አልተከተለኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላወቅሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ደጆቹ በውዳሴ፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፥ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ። |
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፥ “አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ በጕልበታቸውም ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ደግሞም ለንጉሡ።
እነሆ፥ የባሪያዎች ዐይኖች ወደ ጌቶቻቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም ይቅር እስከሚለን ድረስ ዐይኖቻችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
እግዚአብሔር እርሱ አምላካችን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፥ እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያውም በጎች ነን።
በእግዚአብሔር የተሰበሰቡም ይመለሳሉ፤ በደስታም ተመልሰው ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘለዓለም ደስታም በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታንም ያገኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘንና ትካዜም ይጠፋሉ።
በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን?