እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የኃጥኣን መንገድ ግን ትጠፋለች።
እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ይጠብቃልና፤ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።
ጌታ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።
ስለዚህ እግዚአብሔር የጻድቃንን አካሄድ ያውቃል፤ የክፉ ሰዎች አካሄድ ግን የሚያመራው ወደ ጥፋት ነው።
መንገዴን ፈጽሞ ዐወቀ፥ እንደ ወርቅም ፈተነኝ
ጠላት ነፍሴን ከብቦአታልና ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አዋርዶአታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኖሩኝ።
ሰውነቴ በላዬ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
ለእንስሶችና ለሚጠሩት ለቍራዎች ጫጩቶች፥ ምግባቸውን የሚሰጣቸው እርሱ ነው።
ጠላቶች በጦር ለዘለዓለም ጠፉ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥ ዝክራቸውንም በአንድነት ታጠፋለህ።
በሰዎች ዘንድ ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን ወደ ሲኦል ጕድጓድ ታደርሳለች።
የክፉዎች መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ ጽድቅን የሚከተሉትን ግን እግዚአብሔር ይወድዳቸዋል።
እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።
“በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና፤ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን መንጋዎችን አውቃለሁ፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል።
የእኔ የሆኑ በጎች ግን ቃሌን ይሰሙኛል፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል።
ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።
እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤
ለሚጸልይ ጸሎቱን ይሰጠዋል፤ የጻድቃንን ዘመን ይባርካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይደለምና።