ምሳሌ 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮችዋን ልካ በከፍተኛ ዐዋጅ ወደ ማዕድዋ ጠራች። እንዲህም አለች፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴት አገልጋዮቿንም ላከች፤ ከከተማዪቱም ከፍተኛ ቦታ ተጣራች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶች አገልጋዮችዋን ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገረዶችዋም በከተማው ከፍተኛ ቦታ ላይ ቆመው፥ |
ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥበቡ እንዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም።
ለምሳ የተጠሩበትም ቀን በደረሰ ጊዜ የታደሙትን ይጠራቸው ዘንድ አገልጋዩን ላከ፤ እርሱም ሄዶ የታደሙትን፦ አሁን ምሳውን ፈጽመን አዘጋጅተናልና ኑ አላቸው።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “እኔ ለዓለም በግልጥ ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብም፥ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም የተናገርሁት አንዳች ነገር የለም።
በኋለኛዪቱ በታላቅዋ የበዓል ቀንም ጌታችን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “የተጠማ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።