ዮሴፍም ብንያምን ከእነርሱ ጋር በአየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “እነዚያን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው፤ እርድም እረድ፤ አዘጋጅም፤ እነዚያ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።”
ምሳሌ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋንም በማድጋዋ ጨመረች። ማዕድዋን አዘጋጀች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍሪዳዋን ዐረደች፤ የወይን ጠጇን ጠመቀች፤ ማእዷንም አዘጋጀች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን አዘጋጀች፥ ማዕድዋን አሰናዳች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላዘጋጀችውም ግብዣ ፍሪዳ ዐረደች፤ የጣፈጠ የወይን ጠጅም ጠመቀች፤ ገበታም ዘርግታ ማእድ ሠራች። |
ዮሴፍም ብንያምን ከእነርሱ ጋር በአየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “እነዚያን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው፤ እርድም እረድ፤ አዘጋጅም፤ እነዚያ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።”
የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የወይንን ፍለጋ ለሚከተሉስ አይደለምን? ግብዣ ከተደረገ ዘንድ በወይን አትስከሩ፥ ነገር ግን ከደጋግ ሰዎች ጋር በመደማመጥ ተነጋገሩ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝቡ ሁሉ ግብዣን ያደርጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ፤ የወይን ጠጅንም ይጠጣሉ፤ ዘይትንም ይቀባሉ።