በቤቷ ደጅ በአደባባይ በወንበር ላይ በግልጥ ተቀምጣ፥
በቤቷ ደጃፍ ላይ ትጐለታለች፤ በከተማዪቱ ከፍተኛ ቦታ በመቀመጫ ላይ ትቀመጣለች።
በቤትዋ ደጅ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ በወንበር ላይ ትቀመጣለች፥
እርስዋ በቤትዋ በር ላይ ወይም በከተማው ከፍተኛ ቦታ ላይ ትቀመጣለች፤
መንገድህን ከእርስዋ አርቅ፥ ወደ ቤቷም ደጅ አትቅረብ፥
በተራሮች ጫፍ ላይ ናትና፥ በጎዳና መካከልም ትቆማለች።
በመንገድ የሚያልፉትን አካሄዳቸውንም ያቀኑትን ትጠራለች።
አገልጋዮችዋን ልካ በከፍተኛ ዐዋጅ ወደ ማዕድዋ ጠራች። እንዲህም አለች፦
በየመንገዱ ራስ ከፍ ያለውን ቦታሽን ሠራሽ፤ ውበትሽንም አረከስሽ፤ ለመንገድ አላፊም ሁሉ እግርሽን ገለጥሽ፤ ዝሙትሽንም አበዛሽ።