የተወደደች ነገርን እናገራለሁና ስሙ፤ ከከንፈሮቼም ቅን ነገርን አወጣለሁ፤
የምናገረው ጠቃሚ ነገር ስላለኝ አድምጡኝ፤ ቀና ነገር ለመናገር ከንፈሮቼን እከፍታለሁ።
ክቡር ነገርን እናገራለሁና ስሙ፥ ከንፈሮቼም ቅን ነገርን ለመናገር ይከፈታሉ።
የምናገረው ቁም ነገር ስላለኝ አድምጡ፤ ከአንደበቴ ትክክለኛ ነገር ይወጣል።
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል። አምላካችንም ዝም አይልም፤ እሳት በፊቱ ይነድዳል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ።
በከንፈሮችህ ቃሌ ብትኖር ለከንፈሮቼ የቀኑ ይሆናሉ።
መልካም ስጦታን እሰጣችኋለሁና፥ ሕጌን አትተዉ።
እግዚአብሔር የተናገረውን፥ ዓለም ሳይፈጠር፥ ሰውም ሳይፈጠር ተሰውሮ የነበረውን ምክሩን እፈጽም ዘንድ።