ምሳሌ 8:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለባሕር ድንበርን በከለለ ጊዜ፣ ውሆችም የርሱን ትእዛዝ እንዳያልፉ፣ የምድርንም መሠረቶች ወሰን ባበጀ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት በመሠረተ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባሕር ውሃዎች ከተመደበላቸው ስፍራ በላይ ከፍ እንዳይሉ ባዘዛቸው ጊዜ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ እኔ እዚያ አብሬው ነበርኩ። |
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢትረፈረፍና ቢጮኽ ከእርሱ አያልፍም።