ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥ ማስተዋልንም፦ “ወዳጄ” ብለህ ጥራት፥
ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም፣ “ዘመዴ ነህ” በለው፤
ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥ ማስተማውልንም፦ “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፥
ጥበብን እንደ እኅትህ፥ ማስተዋልንም እንደ ቅርብ ወዳጅህ አድርገህ ቊጠራቸው።
ሞትን፦ አንተ አባቴ ነህ አልሁት፤ ትሎችንም እናንተ እናቴም ወንድሞቼም ናችሁ አልኋቸው።
በጣቶችህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላትም ጻፋቸው።
ከባዕድና ከክፉ ሴት ዋዛ ነገርንም ከምታመጣብህ ትጠብቅህ ዘንድ።
ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ የእናቴን ጡት ትጠባ ዘንድ ማን በሰጠህ? በሜዳ ባገኘሁህ ጊዜ በሳምሁህ፥ ማንም ባልናቀኝም ነበር።